ለአርጎባ ልዩ ወረዳ ጋቸኒ ከተማ የጎዳና መንገድ መብራት ዝርጋታ የተቀረፀ ፕሮፖዛል

ብርሃን ለሁሉ

አዘጋጅ: የአርጎባ ልዩ ወረዳ መሬ/አስ/ከተ/ልማ/ኮን/ጽ/ቤት

ጋቸኒ | ታህሳስ 2016 ዓ.ም

መግቢያ

የጋቸኒ ከተማ በአፋር/ብ/ክ/መን/ በአርጎባ ልዩ ወረዳ የምትገኝ ከተማ ስትሆን የወረዳዋ መናገሻ በመሆኗ በክልሉ የንዑስ መዘጋጃ መስፈርትን በማሟላት የንዑስ መዘጋጃ ከተማ በመሆን የከተማነት ግስጋሴ ላይ ትገኛለች:: የጋቸኒ ከተማ በከተማ ደረጃ በመቋቋም የቅርብ አመታት እድሜ ያስቆጠረች ብትሆንም የከተማዋ እድገት በዚህ አጭር ጊዜ ውስጥ ውጤታማ ስራዎችን በመስራት ጥሩ ደረጃ ላይ እንድትገኝ አድርጓታል :: ከተማዋ በ1998 ዓ.ም የመብራት አገልግሎት ያገኘች ሲሆን ከዚህ ጋር በተያይዞ በቅደም ተከተል የቴሌ አገልግሎት በማግኘት እንዲሁም በ2015 ዓ.ም የብሮድባንድ ኢንተርኔት wifi እና ባለ ገመድ የቤት ስልክ አገልግሎት እንድታገኝ ተደርጓል::

በዚህም ምክንያት የማህበረሰቡን የኑሮ ሁኔታ በማሻሻል እና ማንኛውንም information (ለኢንፎርሜሽን) ቅርብ እንዲሆኑ የሚረዳ እንደመሆኑ መጠን ከፍተኛ ስራ ተሰርቷል:: የጋቸኔ ከተማ አገር አቋራጭ ረጅም ከአዋሽ አርባ ደብረብረሃን የሚያገናኘው የአስፓልት መንገድ በከተማዋ መሃል የሚያልፍ በመሆኑ ለከተማዋ እድገት ከፍተኛ ሚና ይጫወታል::  የከተማዋ የህዝብ ብዛት ወደ 15000 (አስራ አምስት ሺህ) የሚጠጋና ከዚህ ውስጥ ከ65 በላይ የሚሆነው ወጣት እንደሆነ ዳታዎች ያሳያሉ::

ከተማዋ በመስፋት ላይ ያለች እንደመሆኑ መጠን በከተማዋ ውስጥ ባሉ የተለያዩ ደረጃቸውን የጠበቁ መሰረተ ተቋማት  ኢማም አህመድ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት፣ የሰአደዲን ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ፣ እንዲሁም ወደ ጋቸኒ አጠቃላይ ጤና አጠባበቅ ጣቢያ የኒወስዱ መንገዶች መብራ ባለመኖሩ ለተጠቃሚዎች አስቸጋሪ ሆኖ ቆይቷል፡፡

ጋቸኒ ጤና ጣቢያ እና ዋናው መንገድ እንዲሁም ወደ ሙዚየም የሚወስዱ መንገዶች የመንገድ ላይ መብራት ባለመኖሩ በጋቸኒ ከተማ የሚኖሩ ማህበረሰብ ክፍሎች በብዛት አገልግሎት የሚሠጡ መንገዶች በመሆናቸው በምሽት ሠዓት ለመንቀሳቀስ ለደህንነታቸው ስጋት ስለሆነባቸው ማህበረሰቡን ከስጋት ለማላቀቅ ብሎም የከተማዋ ውጫዊ ገጽታ ድምቀት የሚሰጣት በመሆኑ ይህ የጎዳና መንገድ መብራት ዝርጋታ አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ ይህ ፕሮፖዛል ተዘጋጅቷል፡፡

ችግሮች

የሚታዩ ችግሮች

የጋቸኒ ከተማ ፕላኗን በመጠበቅ እየተገነባች ያለች ከተማ ብትሆንም በከተማዋ ዋና ዋና መንገዶች ላይ የመንገድ መብራት ባለመኖሩ ማህበረሰቡ በምሽት እንደፈለገው መንቀሳቀስ እንዳይችል አድርጎታል፡፡ ይህንን ችግር ለመፍታት በወረዳው የመሬት አስተዳደር ከተማ ልማት ኮንስትራክሽን ፅ/ቤት የበጀት ውስንነት ያለበት በመሆኑ ለችግሩ መፍትሄ መስጠት እንዳይችል አድርጎታል:: 

የችግሩ መፍትሄ

በጋቸኔ ከተማ ዋና ዋና መንገዶች የመንገድ መብራት ችግር ለመቅረፍ እና መፍትሄ ለመስጠት የወረዳዋ የመሬት አስተዳደር ከተማ ልማት ኮንስትራክሽን ፅ/ቤት ለማከናወን የሚያስችል የበጀት ውስንነት ያለበት በመሆኑ እንዲሁም ከከተማዋ በመዘጋጃ የሚሰበሰብ ገቢ ዝቅተኛነት የመንገድ ላይ መብራትን ተግባራዊ ለማድረግ ከአቅም በላይ በመሆኑ የወረዳዋ ከተማ ልማት ኮንስትራክሽን ፅ/ቤት  ይህን ፕሮጀክት በመቅረፅ ድጋፍ በማፈላለግ ለመተግበር በማለም አቅዶ በመንቀሳቀስ ላይ ይገኛል:: በዚህም መሰረት የተቀረፀው ፕሮጀክት ለችግሩ መፍትሄ መልስ የሚሰጥ በመሆኑ መልካም እገዛችሁን በመሻት ለምንጠይቀው ጥያቄ መልካም ምላሽ እንደምናገኝ ተስፋ እናደርጋለን::.

ፕሮጀክት

የፕሮጀክቱ አስፈላጊነት

 የዚህ ፕሮጀክትአስፈላጊነት ዋና ዋና ምክንያቶች በየጊዜው እየጨመረ የሚገኘው የከተማዋ እድገት ጋር ተያይዞ የህዝብ ቁጥር በመጨመሩ እንዲሁም ከአዋሽአርባ-ደብረብርሃን የተገነባው የአስፋልት መንገድ ለዕድገቷ ትልቅ አስተዋጽኦ ከማበርከቱ ጋር ተያይዞ የከተማዋ ማህበረሠብ በምሽት ለተለያዩ ጉዳዮች የሚያደርጉት እንቅስቃሴ ማለትም ለንግድ፣ ወደ ተለያዩ ተቋማት፣ ከሌላ አካባቢ ወደ ከተማዋ ለሚገቡ እንግዶች በመጨመሩ የመንገድ ላይ መብራት የግድ አስፈላጊ ሆኖ አግኝተነዋል፡፡ ስለዚህ ይህን ተግባራዊ ለማድረግ የወረዳውም በጀት ሆነ የከተማዋ ገቢ የአቅም ውስንነት ያለበት በመሆኑ ይህን ፕሮጀክት በመቅረጽ ድጋፍ በማፈላለግ ተግባራዊ ማድረግ አላማ አድርጎ መሆኑን መገንዘብ አስፈላጊ ነው እንላለን፡፡

የፕሮጀክቱ አላማ

ይህን ፕሮጀክት ለማዘጋጀት ያስፈለገበት ዋነኛ ምክንያቶች በየጊዜው የከተማዋ መስፋፋት ጋር ተያይዞ እየጨመረ የመጣው የማህበረሰብ ቁጥር መጨመር በምሽት የሚደረጉ እንቅስቃሴዎች እንዲፈጠር አድርጓል፡፡ ስለዚህም የወረዳው የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ጽ/ቤት ይህን በምሽት የሚደረግ እንቅስቃሴ ደህንነቱ የተጠበቀ እና ሰላማዊ በሆነ ሁኔታ መንቀሳቀስ እንዲቻል ለማድረግ በጀት በመያዝ የጎዳናዎች የመንገድ መብራት ግንባታ   ማድረግ የሚያስችል አቅም የሌለው በመሆኑ ይህን ፕሮጀክት በመቅረጽ ድጋፎችን በማፈላለግ ዋና አላማ አድርጓል፡፡ በዚህም ምክንያት ዋናው በከተማዋ የሚያልፈው የአስፋልት መንገድ፣ ወደ ጤና ጣቢያ የሚወስደው መንገድ፣ ወደ 1ኛ ደረጃ ት/ቤት የሚወስደው መንገድ፣ወደ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት የሚወስደው መንገድ እና ወደ ሙዚየሙ መልኩ ችግሮቹን ለመቅረፍ እንዲቻል የተነሳለትን አላማ ተግባራዊ ለማደረግ ለጥያቄው መልካም ምላሽ እንደሚያገኝ ተስፋ ያደርጋል፡፡

የፕሮጀክቱ ተጠቃሚዎችን በተመለከተ በሽተኞችን ወደ ጤና ጣቢያ ይዘው ለሚንቀሳቀሱ የማታ ትምህርት ለሚማሩ ተማሪዎች በዋናው የአስፋልት መንገድ ለሚደረጉ የንግድ እና የተለያዩ እንቅስቃሴ እና ወደ ተቋም እንዲሁም ወደ ሙዚየም ለሚደረጉ እንቅስቃሴዎች በአጠቃላይ ተጠቃሚ የሚያደርግ ሲሆን ከዚህ በተጨማሪ በሠላም እና ፀጥታው ዙሪያ ወንጀልን ከመከላከል አንጻር የሚሰጠው ጥቅም ቀላል እንዳልሆነ ግልፅ ሲሆን ከዚህ ባሻገር ከሌላ አካባቢ ወደ ከተማዋ በምሽት የሚደርሱ ሠዎች ሳይደናገሩ በመንገድ መብራቶቹ አማካኝነት የሚፈልጉበት ቦታ መድረስ እንዲችሉ የሚረዳ በመሆኑ ጥቅሙ ለተጠቃሚዎች የትየለሌ እንደሆነ ግልጽ ነው፡፡

  • ፕሮጀክቱ ከተፈቀደ በኋላ የዋጋ ጭማሪ ከተከሠተ
  • የጊዜ አጠቃቀም መጓተት
  • ከጥራት ጋር በተያያዘ ጥያቄ የሚያስነሳ ከሆነ
  • በከተማዋ ያልተካተቱ መንገዶች አካባቢ በሚኖሩ የማህበረሰብ ክፍሎች ጥያቄ ሲነሳ
  • በስራው ክንዋኔ ላይ አደጋዎች ቢፈጠሩ
  • የጨረታ ክንዋኔ ፍትሃዊነት ላይ ሊነሱ የሚችሉ ጥያቄዎቸ
  • የትራንስፖርት ችግር
  • በዋጋ ግሽበት ለሚፈጠሩ የበጀት እጥረት ከወረዳዋ መንግስት ጋር በመነጋገር ለችግሩ መፍትሄ የማመቻቸት ሁኔታ መፍጠር
  • ጨረታውን ያሸነፈው አካል በውሉ መሰረት እንዲያስረክብ ክትትል እና ግምገማ ማካሄድ
  • ጥያቄ ሊያስነሱ የሚችሉ ችግሮችን ጥንቃቄ መወሠድ እንዳለበት ታውቆ በእቅዱ መሠረት እንዲመራ ማድረግ
  • የኛ መንገድ አልተካተተም በማለት ለሚያነሱ የማህበረሰብ ክፍሎች ይህ ፕሮጀክት ከመጀመሩ በፊት ማህበረሠቡን በመሰብሰብ በማወያየት ወደፊት ለሁሉመ ተደራሽ እንደሚሆን ማስረዳት
  • ለሚፈጠሩ አደጋዎች ቅድመ ጥንቃቄ በማድረግ እርምጃ መውሰድ በተጨማሪም ክትትል በማድረግ ጥራቱን የጠበቀ ስራ እንዲሰራ ማድረግ
  • የጨረታ አወጣጥ ስርዐቱ ህግን ተከትሎ መፈጸም ያለበት ሲሆን የወል እና ጨረታ ስራን የወረዳዋ የመሬ/አስ/ከተ/ል/ኮን/ጽ/ቤት በመተግበር የፍትሃዊ የጨረታ ሂደቶች እንዲፈጸሙ ክትትል በማድረግ ይሠራል
  • የትራንስፖርት ችግርን ከመንግስት ጋር በመነጋገር የሚፈታ ይሆናል

ከአርጎባ ልማት ማህበር/ከአ.ል.ማ/ ድጋፍ በማፈላለግ የሚሰራ ይሆናል

የአረጎባ ልዩ ወረዳ መሬት አስተዳድር ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ፅ/ቤት

የአርጎባ ልዩ ወረዳ የወረዳዋ ዋና መቀመጫ እና መናገሻ በሆነችው በጋቸኒ ከተማ

 ከዚህ በታች በሰንጠረዥ በየደረጃው፣ በአይነት፣ መለኪያ እና መጠን የሚያስፈልገው የገንዘብ ዝርዝር አጠቃላይ ወጪዎች እንደሚከተለው ቀርቧል፡፡ ለጋቸኒ ከተማ የጎዳና መንገድ መብራት የሚያስፈልግ በጀት/ገንዘብ የዋጋ ተመን /street light specificationand bill of quantities

 

የስራ መግለጫ/Work Discription

 

የምድር ስራ እና የአርማታ ስራ መጠን/Earth work and concrete work quantities

ተ.ቁ

ዝርዝር ተግባራት

መለኪያ

መጠን

ነጠላ ዋጋ

ጠቅላላ ዋጋ

1

ማቆሚያ/Concrete wall

ጥልቀት 1.5m ስፋት 0.7m*0.7m 

𝑚3

42.4

562.35

23,843

2

የቦይ ቁፋሮ  የመብራት ዝርጋታ እስከሚሸፍነው

PVC Pipe

ስፋት 30*50 cm2  ጥልቀቱ 2120cm

𝑚3

458

250

114,500

3

Concrete ለሞሙላት ከስራ ቦታ ላይ የመቁረጥና የማስተካከል ስራዎች

 

𝑚3

342

300

102,600

4

Compaction/የመጠቅጠቅ

ስራ c-25 concrete type

 

𝑚3

5.4

2500

13,500

5

Man hole የውስጠኛው ከፓወር-መስመር በ HBC የሚሸፈን ሲሆን የላይኛው ደግሞ በ Concrete የሚሸፈን ይሆናል

Man hole ስፋት

50cm*50cm

For maintenance

40cm*40cm*50cm

 

 

𝑚3

31.1

6200

192,820

6

ጠቅላላ ዋጋ/Total price

 

𝑚3

 

 

447,263

 

 

 

 

የስራ መግለጫ/Work Discription

 

 

የመካኒካል ስራ መጠን/mechanical work quantities

 

ተ.ቁ

ዝርዝር ተግባራት

 

መለኪያ

መጠን

ነጠላ ዋጋ

ጠቅላላ ዋጋ

1

ዋና ቋሚ ብረት/single arm galvanized pole

ርዝመት 9m  ቁመቱ 3mm የሆነ

pcs

50

31120

1,556,000

2

ጠቅላላ ዋጋ/Total price

 

 

 

 

1,556,000

 

የስራ መግለጫ/Work Discription

 

 

የኤሌክትሪካል የስራ መጠን/ electrical work quantities

 

 

ተ. ቁ

ዝርዝር ተግባራት

 

መለኪያ

መጠን

ነጠላ ዋጋ

ጠቅላላ ዋጋ

1

LED Street light SMD type

150w

Lens 165-280v 50Hz aluminum + timber glass  

Pcs

60

6300

378,000

2

Ethiopian ground cable

Area 4mm*16mm

m

2.142

550

1,178.1

3

Pac shoul led Ethiopian cable 

Area 3mm*2.5mm

m

620

310

192,200

4

Parallel connecter  

8 with 50mm*380

resister 

Pcs

30

120

3,600

5

Plastic PVC electric cable

50

m

1.96

60

117.6

6

Plastic PVC For erect to connecter 

25

m

70

25

1,750

7

Control switch 

16A As 15-216E-

Photo control

Pcs

2

3,100

6,200

8

Manual Breaker

ABB32A

Pcs

1

1,400

1,400

9

Fix fuse 

16A

Pcs

105

280

29,400

10

Fix fuse holder

ABB32A

Pcs

65

550

3,5750

11

Rod copper cold steel

16mm and 1.5m quality copper

Pcs 

4

24,000

96,000

12

Installation MDB-40 street light pillar board control panel PGH conductor 504 molded

breaker  

ABB125A light sensor PGH concrete work

40cm*20cm*50cm

Pcs 

2

15,250

30,500

13

Supply and installation 

ELPA 3 phase

24kw power

Pcs 

2

180,000

360,000

14

Monitoring and evaluation town construction office 

 

Pcs 

12

 

454,000

15

ጠቅላላ ዋጋ/Total price

 

 

 

 

4,992,095.7

 

የምድር ስራ እና የአርማታ ስራ ወጪ= 447,263 ብር

የመካኒካል ስራ ወጪ =1,556,000ብር  

የኤሌክትሪካል ስራ ወጪ= 4,992,095.70 ብር

ጠቅላላ ድምር = 6,548,542.96 ብር

  • በመሬት/አስ/ከተ/ልማ/ኮን/ጽ/ቤት አማካኝነት የጨረታ ውል አፈጻጸም ህግ እና ስርዐቱን በጠበቀ መልኩ ፍትሃዊ አሰራርን በመተግበር ጨረታ በማውጣት ለአሸናፊው በመስጠት ተግባታዊ ያደርጋል
  • ስራው እስኪጠናቀቅ ድረስ በመከታተል ጥራት ያለው ስራ እንዲተገበር ይሠራል
  • በተቀመጠው ጥናት መሰረት ተግባራዊነቱን ያረጋግጣል
  • የተገኘውን ድጋፍ በአግባቡ ስራ ላይ እንዲውል ጠንክሮ በመስራት ተፃሚነቱን ያረጋግጣል
  • ከወረዳዋ ከሚመለከታቸው አካል ጋር በጋራ ይሠራል
  • ማህበረሰቡን የሚጎዳ ችግር እንዳይፈጠር ጥንቃቄ የተሞላበት ስራ እንዲሰራ በባለሙያዎች ክትትል በተጠናከረ ሁኔታ እንዲፈፀም ይሰራል
  • ስራው ተጠናቅቆ አገልግሎት መስጠቱን ያረጋግጣል
  • ፍትሃዊ አሠራርን በተከተለ መተግበሩን ለሚመለከተው አካል ያሳውቃል
  • የነበሩ ችግሮች ተፈተው ማህበረሰቡ በፈለገው ሰዐት በምሽት መንቀሳቀስ መቻሉን ያረጋግጣል
  • በምሽት የከተማዋ ውበት ከጨለማ ወደ ብርሃን መቀየር መቻሉን ሰርቶ በማሳየት ያረጋገጣል
  • ስራው ሳይንጓተት በጊዜ እንዲጠናቀቅ በማድረግ ውጤት ማምጣቱን በማረጋገጥ መተግበሩ የሚጠበቅ ሆኖ አገልግሎቱ ለተያዘለት ዓላማ ብቻ መዋሉን ያረጋግጣል::

የክትትልና በመዘርጋት የወረዳዋ መሬ/አስ/ከተ/ልማ/ኮንስ/ጽ/ቤት በጽ/ቤቱ ያሉትን ባለሙያዎች በመጠቀም የሚከታተል እና ሪፖርት በየጊዜው በመቀበል የሚሰራ ይሆናል፡፡ በየጊዜውና በየሰአቱ ስራውን በመከታተልየስራውን ተፈፃሚነትበማረጋገጥ ፅ/ቤቱ ተግባራዊ የሚያደርግ ሲሆን በስራዎቹ ላይ ለሚፈጠሩ ችግሮች የፅ/ቤቱ ሃላፊ እንደየአስፈላጊነቱ እርምጃ ይወስዳል፡፡

የክትትልና ግምገማ ስርዐቱ ስራው በተያዘለት የጊዜ ገደብ እንዲጠናቀቅ ፍትሃዊ አሠራርን የሚከተል ሲሆን አጠቃላይ ውጤቱን ለድጋፍ አድራጊው ሪፖረት ያደርጋል ከዚህ ባለፈ ከከተማዋ የመዘጋጃ ስራ አስኪያጅ ፅ/ቤት ጋር በጋራ በመስራት ለወረዳዋ ለሚመለከተው አካል ሪፖርት ያደርጋል፡፡

የጋቸኒ ከተማ የቱንም ያክል ከተማዋ ብዙ እድሜ ባታስቆጥርም በዙሪያዋ ብዙ ዕድሜ ጠገብ ቅርሶችን የያዘች ከተማ ናት፡፡ ከነዚህም ውስጥ ከ 600 ዓመት በላይ እድሜ ያስቆጠሩ መስጊዶችና መቃብሮች ይገኙበታል፡፡ ከተማዋ በተፈጥሮ ከመታደሏም በላይ በአጭር ጊዜ ወደ እድገት ማማ እየወጣች የምትገኝ ከተማ ስተሆን የአርጎባን ታሪክ የሚያስረዳ እና በውስጡ የአርጎባ ህዝብ/ከሺ ዓመታት በላይ የሆናቸው በሴቶች የተፃፉ ኪታቦችን የወንዶችን ጨምሮ ለጉብኝት እንዲበቃ የሙዚየም ግንባታ ለመገንባት የመሠረት ድንጋይ ተጥሎባት የምትገኝ ከተማ ናት፡፡ የአርጎባ ህዝብ መኩሪያ መናገሻ ከተማ እንደመሆኗ መጠን ውብና ምቹ ከተማ መፍጠር አስፈላጊ በመሆኑ ይህን ፕሮፖዛል በመቅረፅ የመንገድ መብራት ገንባታውን ተግባራዊ ለማድረግ እየተንቀሳቀሰ በመሆኑ ይህን ድጋፋችሁን በማድረግ የታሰበው አላማ ግብ እንዲመታ ትብብር ታደርጉ ዘንድ ይጠይቃል፡፡ 

ይህ ፕሮጀክት አስፈላጊ የጎዳና መንገድ መብራት በሚጠይቀው መሠረት በዝርዝር የቀረበው የገንዘብ መጠን ከዚህ የተሻለ የሶላር ዕድል የዋጋ ቅናሽ የሚሰጥ ከሆነ የቀረበውን ዝርዝር ወጪ በመከለስ የሶላር አማራጮችን መጠቀም እንዲቻል በተቀረፀው ፕሮጀክት ታሳቢ የተደረገ መሆኑነ በመገንዘብ  የሚጠይቅ ይሆናል፡፡